ሊሴ ፓሴ ለማመልከት

  • የአገልግሎት ግዜውን ያበቃ ፓስፖርትዎ ለማሳደስ በቂ ጊዜ ከሌለዎትና በተለያየ አስቸኳይ ምክንያት ወደ አገርቤት ለመጓዝ ከፈለጉ ሌሴ ፓሴ መጠየቅ ይችላሉ፡፡
  • ሊሴ ፓሴው ለአንድ ጊዜ ወደ ኢትዮጵያ መግቢያ ብቻ የሚያገለግል በመሆኑ ሲመለሱ ከኢትዮጵያ ፓስፖርት ማውጣት እንዳለብዎ አይዘንጉ፡፡
  • የፓስፖርትና የሊሴ ፓሴ ማመልከቻ በአንድ ላይ ማቅረብ ወይም የፓስፖርትዎ ማመልከቻ ከኤምባሲው ወደ አገር ቤት ከተላከ ከአንድ ወርና ከዚያ በላይ ሳይሆን ሊሴ ፓሴ ማመልከት አይቻልም። ነገር ግን ኢምባሲው ማመልከቻዎን አገር ቤት ከላከ አንድ ወርና ከዚያ በላይ ከሆነና ፓስፖርቱን ሳይረከቡ የጉዞዎ ቀን ከደረሰ ሊሴ ፓሴ ወስደው አገር ቤት ሲደርሱ የከፈሉበትን ፓስፖርት ከኢሚግሬሽን መረከብ ይችላሉ።

መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች

1. ሁለት የፓስፖርት መጠን ያለውና ቢያንስ ከ6ወር ወዲህ የተነሱት ፎቶግራፍ (ሁለቱ ጆሮዎች የሚታዩ፣ መደቡ ነጣያለና ከጀርባው ስም የተጻፈበት)

2.  አገልግሎቱ ያበቃዉን ፓስፖርት መረጃ ያለበትን ማለትም ስም፣ ፎቶግራፍ፣ ፓስፖርቱ የተሰጠበትና ለመጨረሻ ጊዜ የታደሰበትን ገጽ የሚያሳይ ኮፒ ማቅረብ

3.  ፓስፖርትዎ ከጠፋ የትና መቼ እንደወሰዱት የሚገልጽ ማስታወሻ እንዱሁም በኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተረጋገጠ የልደት ማስረጃ ኮፒ ማቅረብ4 የአገልግሎት ክፍያ $50.00 ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ የባንክ የክፍያ ደረሰኝ መሆን ይኖርበታል፡፡5መጠየቂያ ቅጽ መሙላት (click here to download FORM)