የውክልና አገልግሎት

እባክዎ አገልግሎቱን አዘጋጅተን እንድንስጥዎ በጥንቃቄ አንብበው አስፈላጊውን ማስረጃዎች ከነ ቅጅ (Photo Copy) አያይዘው ያቅርቡ/ይላኩ፡፡
 • ዜግነትዎ ኢትያጵያዊ ከሆነ ወይም ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኖሮዎት
  • ኤምባሲው ዘንድ በአካል የሚቀርቡ ከሆነ የውክልና ሰነዱን ኦፊሰሩ ባለበት ፈርመው ማስፈፀም ይኖርበታል
  • ውክልናው በመልዕክት / mail / የሚልኩ ከሆነ ሰነዱን ኖተራይዝ አድርገው አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፖስታ ከነቴምብሩ አብሮ መላክ ይጠበቅበታል፡፡
 • የሌላ አገር ዜጋ ከሆኑ ወይም በትውልድ ኢትዮጵያዊ  መታወቂያ ካርድ ከሌለዎት ወይም አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት ከሌለዎት፡-
  • ውክልናውን በአማርኛና በእንግለሊዘኛ ተጽፎ ኖተራይዝ በማድረግ በመጀመሪያ ባሉበት  በመላክ አረጋግጦ መቅረብ/መላክ
  • አገልግሎቱን በፓስታ ቤት በኩል ለምትጠይቁ አመልካቾች መላኪያዎም ሆነ መመለሻ ፖስታዎ ትራኪንግ ቁጥር ባለው የፖስታ አገልግሎት እንዲጠቀሙ እንመክራለን፡፡
የፖስታ አላላክ መመሪያ

 • በፖስታ ቤት አማካኝነት ውክልና የምትጠይቁ ባለጉዳዮች መላኪያም ሆነ መመለሻ ፖስታ መጠቀም የሚኖርባችሁ Tracking Number ባለው መሆን ይገባዋል፡፡
 • የላኩት ፖስታ ወደ ኤምባሲያችን ለመድረሱ ፖስታውን በላኩበት  የTracking Number በመጠቀም ማወቅ ፡፡
 • የውክልናዎ ማመልከቻ ኤምባሲው ከተረከበት ከሁለት ወይም ከሶስት የስራ ቀናት በኋላ ያለበትን ደረጃ ለማወቅ በላኩት የመመለሻ ፓስታ Tracking Number በመጠቀም ያጣሩ!
 ሀ የአትዮጵያዊ ዜግነት ላላቸው
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1 ውክልናውን አዘጋጅቶ ማቅረብ/መላክ
2 የታደሰ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ኮፒ
3 የአገልግሎት ክፍያ $62 ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ የባንክ ደረሰኘ
 4 የመጠየቂያ ቅጽ መሙላት (Click here to download a Form)
5 ውክልናውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው መላክ
ለ. ትውልደ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ለያዙ
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1 ውክልናውን አዘጋጅቶ ማቅረብ/መላክ
2 የታደሰ ትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ ካርድ ኮፒ
3 የአገልግሎት ክፍያ $62 ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ የባንክ ደረሰኘ
4 የመጠየቂያ ቅጽ መሙላት(Click here to download a Form)
5 ውክልናውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው  መላክ
ሐ. የሌላ አገር ዜጋ ለሆኑ ወይም በትውልድ ኢትዮጵያዊ  መታወቂያ ካርድ ለሌላቸው ወይም አገልግሎቱ የፀና የኢትዮጵያ ፓስፖርት የሌላቸው
መሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች
1 በአማርኛና በእንግሊዝኛ ጽፈው ያዘጋጅቱን ውክልና በመጀመሪያ ባሉበት አገባብነት  ካለዉ የመንግሰት አካል ቀጥሎ በአንካራ በሚገኘው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በመላክ አረጋግጦ ማምጣት
2 የአገልግሎት ክፍያ $95 ዶላር ለኢትዮጵያ ኤምባሲ የተፃፈ የባንክ ደረሰኘ
3 የመጠየቂያ ቅጽ መሙላት(Click here to download a Form)
4 ውክልናውን በፖስታ ቤት በኩል የሚልኩ ከሆነ ፣ አድራሻዎ የተጻፈበት መመለሻ ፓስታ Tracking Number ያለው  መላክ